Skip to main content
wer

ሆሣዕና የትምህርት ኮሌጅ የ 2018 በጀት የግማሽ ዓመት (የ 6ወራት) የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በኮሌጁ ማናጅመንት አባላት ተገምግሟል። (ሆሣዕና የትምህርት ኮሌጅ ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም ) የኮሌጁ ዋና ዲን ዶ/ር አባይነህ ኤርጎጎ ባለፉት ስድስት ወራት በአካዳሚክ እና በአስተዳደር ዘርፍ በዕቅድ የተያዙ በርካታ ተግባራት በውጤታማነት የተከናወኑ መሆኑን በሪፖርቱ አቅርበው በሁሉም የጋራ ርብርብ የተገኙ ውጤቶች መሆኑን አንስተዋል። 

በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ ለተቋሙ ተልዕኮ መሳካት ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ተግባራት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል። ከቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርት በመነሳት የኮሌጁ ማናጅመንት አባላት ዘርፎቻቸውን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እና ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ሪፓርቱ የኮሌጁን የአፈፃፀም ክፍተቶች በመለየት ለቀሪ ስድስት ወራት አፈጻጸም ትልቅ አጋዥ መሆኑንና በቀጣይም በተቀናጀ ሁኔታ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ የማኔጅመንት አባላት አንስተዋል። 

በመጨረሻም የኮሌጁ ዲን በሪፖርቱ መሰረት የታዩ ጠንካራ ጎኖችና የአፈፃፀም ክፍተቶችን በዝርዝር በመለየት በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በማሳሰብ ውይይቱ ተጠቃልሎአል። ሆሳዕና የትምህርት ኮሌጅ!