Adminhctedu
ሆሳዕና የትምህርት ኮሌጅ በክልሉ በሚገኙ በተለያዩ ት/ቤቶች ለብሄራዊ ፈተነ ተፈታኝ ለሆኑ ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠ ይገኛል። በክልሉ በሁሉም ማዕከላት የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሚረዳ የማጠናከሪያ ትምህርት እንደ መጀመሪያ ሳምንት ሁሉ የ2ኛ ሳምንት ማጠናከሪያ ትምህርት አሰጣጥ በሁሉም የትምህርት አይነቶች ተጠናክረው ቀጥሏል።
ኮሌጁም በመዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ዞኖች ለብሄራዊ ፈተነ ተፈታኝ ለሆኑ ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ዛሬም ለሁለተኛ ሳምንት በሁሉም አከባቢዎች በተጠናከረ መልክ እየሰጠ መሆኑን የኮሌጁ አመራሮች ተዘዋውረው የመስክ ምልከታ አድርገዋል።
ሆሳዕና የትምህርት ኮሌጅ አይሲቲ ዳይሬክቶሬት!