Adminhctedu
በሆሳዕና የትምህርት ኮሌጅ Competency Based Learning and STEAM Education Training ለሳይንስና ሒሳብ ትምህርት መምህራን እየሰጠ ይገኛል። ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የትምህርት ስርዓቶች እየተለወጡ በመሆናቸው ይህ ስልጠና እጅግ አስፈላጊ ነው።
በዚህ ጊዜ የስራ ገበያውም የተለየ ችሎታ እየጠየቀ መጥቷል፤ ተማሪዎችንም ከመደበኛ ዕውቀት ባለፈ ለችግሮች መፍትሔ መግኘት እንድችሉ፤ ፈጠራን ማየት እና በቡድን መስራት የሚችሉ መሆን ይጠበቃልና በዚህ ሁኔታ የSTEAM የማስተማሪያ አቀራረብ ከተለመዱት የትምህርት ዘዴዎች በላይ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ዛሬ በኮሌጃችን ሳይንስና የሒሳብ መምህራን የተዘጋጀው ስልጠና የSTEAM መሠረታዊ መሆናቸውን ለማብራራት፤ ተግባራዊ የማስተማሪያ ስልቶችን ለማጋራት፤ የእርስ በርስ የልምድ ልውውጥ ለማድረግና አዳዲስ አስተሳሰቦችን ለመፍጠር የተዘጋጀ Workshop ነው እየተሰጠ ያለው።
ስልጠናውን ከ04-06/06/2018 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት በጃፓን ሀገር ሰልጥኖ በመጣው በእጩ ዶ/ር አማረኝ ካሳዬ እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትምህርት ቢሮ ለስልጠናው ተወክለው በመጠ ባለሙያ አቶ እንዳለ ታምሬ እየተሰጠ ነው።