Skip to main content
sdc

ታህሳስ 14/2018 ዓ. ም (ሆሳዕና የትምህርት ኮሌጅ) ሆሳዕና የትምህርት ኮሌጅ። የ2018 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ተማሪዎችን እንኳን ዳህና መጣችሁ ፕሮግራም አካሄደ። በእንኳን ዳህና መጣችሁ ፕሮግራም የኮሌጁ ዲን ደ/ር አባይነህ ኤርጎጎ እንኳን ዳህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ተማሪዎች በኮሌጁ ቆይታ ከምንም ነጻ ሆነው ትምህርታቸውን ብቻ እንድከታተሉ አሳስበዋል። የተማሪዎች ጉዳይ ይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር ሙሉጌታ እሪፎ ለተማሪዎቹ መልዕክት ስያስተላልፍ ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ ሌላ አጀንዳና ጉዳይ እንደሌላ በማሳሰብ በተለያዩ ጉዳዮች ውይይቶችና ስብሰባዎች ስደረጉ ኮሌጁ ማወቅ አለበት ብሏል። 

መ/ር ሙሉጌታ እሪፎ አክለውም ተማሪዎች በኮሌጁ ቆይታ የተለያዩ የኮሌጁን ደንብ እና መመሪያ አቅርበውላቸዋል። ምንም እውቀት ኖሮ ስነ-ምግባር ከተበላሻ ከንቱ እንደሆነ በአጽንኦት ገልጿል። የረጅስትራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር ማቴዎስ ብቲሮ ለተማሪዎች ከውጤትና ከተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ጥብቅ ማሳሰቢያ አቅርቧል። በሌላ በኩል የኮሌጁ መምህራን ማህበር መ/ር አጫሞ ቦቄ ልምዳቸውን ለተማሪዎች ስያከፍሉ እንዳሉት ዋነኛ ትኩረታችሁ ትምህርት ላይ ብቻ ይሁን ብሏል። የዛኔ ነው ሀገር የሚለመው፣ የሚያድገው ብሏል። 

ሆሳዕና የትምህርት ኮሌጅ!